ግሪንላንድ ጠቅላላ ተቋራጭ የድርጅቱን የሥራ አቅም ለማሳደግና አገልግሎቱን ለማስፋፋት የሚያግዘውን ዘመናዊ Cat 330GC ኤክስካቫተር ከ42,000,000 (አርባ ሁለት ሚሊዮን) ብር በላይ በሆነ ወጪ ገዝቶ ወደ ሥራ አስገብቷል።
የድርጅቱ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አጥናፉ ሳህሌ እንደገለጹት፣ የዚህ ዘመናዊ ማሽን መገዛት ፋይዳው ዘርፈ ብዙ ሲሆን፣ ድርጅቱ እያሳየ ላለው ፈጣን ዕድገትም ትልቅ ማሳያ ነው። ድርጅቱ ቀደም ሲል ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የማሽነሪ ኪራይ ይጠቀም የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በራሱ ሙሉ ወጪ ይህንን ማሽን መግዛቱ ያለበትን የኪራይ ወጪ በእጅጉ እንደሚቀንስለት ገልጸዋል።
አቶ አጥናፉ አክለውም፣ ይህ አዲስ ማሽን የድርጅቱን የሥራ ፍጥነትና ጥራት ከማሳደግ ባለፈ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ለማህበረሰቡም የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንደሚሆን ተናግረዋል። ድርጅቱ አሁን ባለው አቅም ሳይወሰን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን በመግዛት የማሽን ፍሊቱን (Fleet) ይበልጥ ለማጠናከርና ለሀገር ልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዕቅድ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል። ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት ግሪንላንድ ጠቅላላ ተቋራጭ በትላልቅ የመንገድና የውሃ ሥራዎች ላይ ያለውን ተወዳዳሪነት ይበልጥ የሚያጎለብተው ይሆናል።

