ግሪንላንድ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ75,000,000 (ሰባ አምስት ሚሊዮን) ብር ጠቅላላ ወጪ እያከናወነ የሚገኘውን የካካ-መጫ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሳይት ርክክብ አድርጓል። በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ግንባታ 70 በመቶ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላትም በቦታው ተገኝተው እስካሁን የተከናወኑ ስራዎችን ጎብኝተው ተረክበዋል።

ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለጥራት፣ ለደህንነት እና ለጥንካሬ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል። መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ በአካባቢው ያለውን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፉም በላይ፣ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን በቀላሉ ለገበያ እንዲያቀርቡ በማድረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን እንደሚያነቃቃው ይጠበቃል።

የግሪንላንድ ጀነራል ኮንትራክተር ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ አጥናፉ ሳህሌ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ ቀሪ ስራዎችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እና በጀት በጥራት አጠናቆ ሙሉ በሙሉ ለማስረከብ ድርጅታቸው የተቻለውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አቶ አጥናፉ አክለውም ቡድናቸው በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜትና ቁርጠኝነት ስራውን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ግሪንላንድ ጠቅላላ ተቋራጭ ለማህበረሰቡ ትክክለኛ ለውጥ የሚያመጡ አስተማማኝ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በጥራት ለማቅረብ ያለውን ጽኑ አቋም በድጋሚ ያረጋግጣል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *